drbekelegetamiw.jpg
e-Books

ገጣሚው - የግጥም መድብል - ከበቀለ ብርሃኑ (ዶ/ር)

5.00

እንዳያችሁት ለዚህ የግጥም መድብል የሰጠሁት አርዕስት “ገጣሚው” የሚል ነው፡፡ “ገጣሚው” ብዬ የሰየምኩበትም ምክንያት፣እግዚአብሔር አብ የሕይወታችን ግጥምጥሞሽ ሁሉ ዋና ደራሲ፣አቀናጅና ሠሪ መሆኑን በርከት ያሉት ግጥሞቼ ያሳያሉና ነው፡፡

አዎ እርሱ የሕይወታችን አልፋና ኦሜጋ ነው፡፡ እርሱ የሕይወታችን መጀመሪያና መጨረሻ ነው፡፡ በእርሱ ፊት የማይታወቅና የተሰወረ ታሪክ የለንም፡፡ ንጉሥ ዳዊት “አቤቱ እኔ በአንተ ታመንሁ፣ አንተ አምላኬ ነህ አልሁ፡፡ ርስቴ በእጅህ ነው” (መዝሙር 31፡14-15) ሊል የቻለው ይህ ዕውነታ በኃይል ገብቶት ነው፡፡ ዋናው የሕይወታችን ደራሲ እሱ መሆኑን በግልጽ ለማሳየትም፣ ንጉሥ ዳዊት ስለ አብ እንዲህ ብሏል፡-

Add To Cart
drbekelegetamiw.jpg